Tuesday, July 17, 2007

Min Tej Alenna

Tej Drro Tetan

ሥንዝር ታህል ጭውውት __ (ቄሱና ዲያቆን ለይኩን )5

ጃርትና ውሻ በዚያች የገጠር ከተማ የሚሸሸው ሰው ቢኖር ለይኩን ብቻ :: ጃርት ጦርዋን እያራገፈች ልታባርረው ብትጥርም እስከመሸሻ ጉድጓዷ ድርሰ እያባረረ ይደበድባታል :: የውሻ ጉዳይ ግን ለየት ያለ ነው ::

“” ለምን ውሻ ትጠላለህ ? ውሻ ‘ኮ ታማኝ ነው ‘’ ጠይቆት ነበር አንድ የፍራፍሬ ደንበኛው ::
click 4 amargna

ሥንዝር ታህል ጭውውት __ (ቄሱና ዲያቆን ለይኩን )4

ድክምክም ባለ የካርቶን ጉራጅ ላይ ደመቅ ተደርጎ ''ለይኩን ኢትፍሩት '' ተፅፎ ውጭ ግርግዳ ላይ ተለጥፏል ::

ፍራፍሬ መደብርዋ ጣራና ግርግዳ አይኑራት እንጂ ገበያው መተላለፊያ መንገዱ ላይ በመሆኑ ገበያተኛ አላጣችም :: የሚያልፉን ቆነጃጅት ደግሞ "" ኧረ በፈጠራችሁ ባትገዙም ስንት ስንት ብላችሁ ጠይቁኝ እንጂ ::"" "" የቆንጆ ልጅ ፈገግታ ራሱን የቻለ ዕንቁ ነው "" ይላል የብርቱካን ሙዝ መደሪን አናናስ ንግድ የሰመረለት , ዲያቆን ለይኩን :: አያለፉትም , ይገዙታል ::

የወቅት -ወቅቱን ፍራፍሬና ሸንኮራ አገዳ ገበያ ላይ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ጥሩ ስምን አትርፏል :: ልዩ መስተንግዶውማ , የከተማዋን ወጣት በደበኝነት በጁ አስገብቶታል :: ""ለይኩን ኢትፍሩት "" ከብዙ ሰው አንደበት የማይጠፋ ታላቅ ስም ሆኗል , ልክ እንደ በቀለ ሞላ ሆቴሎች ::

ፍራፍሬ ገዝተው እቤት ለሚወስዱ በኪስ ወረቀት , እዚያው ለሚበሉ ደግሞ በቢላ እየሸነሸነና በላስቲክ ሳህን በማቅረብ የደበኞችን ፍላጎት በማርካት ግንባር ቀደም ስፍራን ይዟል ::

ስራ እያጣደፈው በነበረ ሰአት ነበር እማሆይ ፅጌ ን ከሩቁ ገበያ ሲገበያዩ ያያቸው ::
click here 4 amargna

Wednesday, July 11, 2007

ፍካቷ

ፍካቷ
Posted on July 11th, 2007
(by bati )

ወይ በሃሳብ በገሀድ
አቅራቦቷን ስናይ ,
ውስጠ -ብዙ ብርሃን
የደመቀች ፀሀይ ::

click here 4 amargna

Tuesday, July 10, 2007

Things are Getting out of Hand somewhere



Thax Teme......this clip is just for you.

Golden Day ዘመነ ፀሀይ

Sat Oct 01, 2005 11:53 am
Post subject: Golden Day
(by bati)
ዘመነ ፀሀይ .....
Sitting just by myself
for hours I,
Asking, but couldn't come
to me a single reply.

Crispy air, dark sky
and cloudless,
A bag full of twinkling
stars.
On such a night
watching the dazzling lights,
feeds pleasure
for the voracious eyes.
Asked, but couldn't come
a single reply,
Why? far away the
ዘመነ ፀሀይ .

Tiny-bitty death
called me some what,
So, I let 'em alone
by wishing a very good night.
stars, planets, moon,
and even the sun,
Gotta blessed me
above from heaven,
'Cuse all showed up quick
in my dream again.

Golden Day.......
Hanging on the sky
a cordless machine,
I saw my babe
rollin' up its spin,
At the very moment
she tried it again,
Gold coins poured down
as a heavy rain.

All my childhood streets
have flooded,
With countless coins
made of the finest gold.
people rushed for it
and collected some,
I was right there
sharing my share with 'em.
ክቡራት -ክቡራን
just allow me to say,
I Welcome you all to the
ዘመነ ፀሀይ .

TenKole'gnaWa (wicked) Hibist

Saturday, July 07, 2007

ሥንዝር ታህል ጭውውት __ (ቄሱና ዲያቆን ለይኩን ) ३

ለይኩን ከመከላከል ወደማጥቃት መሸጋገሩ ቄሱን እጅግ አሳሰባቸው :: ከካፖርታቸው ስር አጠር ያለ ቆመጥ መታጠቅ ከጀመሩ ቆዩ :: አንበርብር የተባለው ውሻቸው በተጠንቀቅ ቤታቸውን እንዲጠብቅ ማድረግና ጩኽቱን ከማጨናገፍ ይልቅ '' ያዘው ! ዘንጥለው ! አትልቀቅ ሳጥናኤል ነው !"" በማለት ማበረታት የጀመሩት ከአጋፍሪው አባ ሰላሙ መደብደብ በኋላ ነው ::
click here 4 amargna

Friday, July 06, 2007

ቅድስተ ቅድስቱ

ከልብሽ አለሁኝ
ከቅኔው ማህሌት
ዜማና ዕውቀትሽ
ከሚዘረፍበት
ከቅድስተ ቅድስቱ
ከነብስሽ ልግባና
መንቀዥቀዤ ያክትም
ባንቺ ባንዷ ልፅና ::

click here 4 amargna

Thursday, July 05, 2007

ሥንዝር ታህል ጭውውት __ (ቄሱና ዲያቆን ለይኩን )2

ዲያቆን ለይኩን አስቸጋሪ ልጅ ሆኖ ያደገ አይደለም :: የመልካም ድርጊት ሁሉ ምሳሌ ነው :: ቄስ ፍቅረ ማሪያም እንዲያ ክፉኛ ሲያጉላሉት እንኳ ሳት ብሎት አንዲትም ቀን ክብራቸውን ገፎ አንተ ብሎአቸው አያውቅ :: click here 4 amargna

ሥንዝር ታህል ጭውውት __ (ቄሱና ዲያቆን ለይኩን )1

ቄስ ፍቅረ ማርያም ዲያቆን ለይኩንን በተክሲያን ቅጥር ግቢ የትኛውም ስፍራ ሲያዩት ንዴታቸውን መቆጣጠር ይሳናቸዋል :: የድቁና አገልግሎቱን ትቶ ወደአለም ከሸሸ ጀምሮ የተራ ምዕመን መብት እንዲያገኝ አልፈቀዱም ::

አዎን ! አይናቸው ከዚያ ሁሉ ህዝበ ክርስቲያን እሱን ብቻ አጉልቶ ነው የሚያሳያቸው :: ለይኩን ነገራቸው ክብደቱ በጣም ስለበዛበት ከአይናቸው ለመሰወር ጥረት ወትሮም አልተለየውም ::

click here 4 amargna