Tuesday, July 17, 2007

ሥንዝር ታህል ጭውውት __ (ቄሱና ዲያቆን ለይኩን )4

ድክምክም ባለ የካርቶን ጉራጅ ላይ ደመቅ ተደርጎ ''ለይኩን ኢትፍሩት '' ተፅፎ ውጭ ግርግዳ ላይ ተለጥፏል ::

ፍራፍሬ መደብርዋ ጣራና ግርግዳ አይኑራት እንጂ ገበያው መተላለፊያ መንገዱ ላይ በመሆኑ ገበያተኛ አላጣችም :: የሚያልፉን ቆነጃጅት ደግሞ "" ኧረ በፈጠራችሁ ባትገዙም ስንት ስንት ብላችሁ ጠይቁኝ እንጂ ::"" "" የቆንጆ ልጅ ፈገግታ ራሱን የቻለ ዕንቁ ነው "" ይላል የብርቱካን ሙዝ መደሪን አናናስ ንግድ የሰመረለት , ዲያቆን ለይኩን :: አያለፉትም , ይገዙታል ::

የወቅት -ወቅቱን ፍራፍሬና ሸንኮራ አገዳ ገበያ ላይ በማቅረብ በአጭር ጊዜ ጥሩ ስምን አትርፏል :: ልዩ መስተንግዶውማ , የከተማዋን ወጣት በደበኝነት በጁ አስገብቶታል :: ""ለይኩን ኢትፍሩት "" ከብዙ ሰው አንደበት የማይጠፋ ታላቅ ስም ሆኗል , ልክ እንደ በቀለ ሞላ ሆቴሎች ::

ፍራፍሬ ገዝተው እቤት ለሚወስዱ በኪስ ወረቀት , እዚያው ለሚበሉ ደግሞ በቢላ እየሸነሸነና በላስቲክ ሳህን በማቅረብ የደበኞችን ፍላጎት በማርካት ግንባር ቀደም ስፍራን ይዟል ::

ስራ እያጣደፈው በነበረ ሰአት ነበር እማሆይ ፅጌ ን ከሩቁ ገበያ ሲገበያዩ ያያቸው ::
click here 4 amargna

No comments: