Monday, December 11, 2006

aynsh'na ayneama አይንሽና አይኔማ

funny boxes? click here

አይን መንገዱ ነው
ለቀልብ መናገሻ
መግቢያና መውጫም
መነሻም መድረሻ
ለምን ይረገም
ምነው ምን ባጠፋ
የማጀትሽን ላይኔ
ባሳየ በይፋ

የልብሽ ረመጡን
እንዲሁም የልቤ
ባይኔ በኩል ፈልቆ
ካይንሽ ላይ ማንበቤ
መውደድ ደርሶ ከእኔ
ወዳንቺ መምጣቴ
በአይንሽ እኮ ነው
ውደጂው በሞቴ

ልክየለሽን ደስታ
በዛው ስፍር ክፋቴ
ጭር ብል በልብሽ
ለመከራ ሕልፈቴ
አይንሽና አይኔማ
ህይወትሽ ህይወቴ ::

No comments: