Wednesday, December 13, 2006

qinnatቅናት

funny boxes? click here
የዐይኖችዋ ጉዳይ
ትዕንግርት ለዐይኖቼ
እጆችዋ ወዳጅ
ለምስኪን እጆቼ
አካልዋን ከአካሌ
ፍቅር አስተሳስሮ
ኑሮ ሀ ኑሮን ሁ ...
ፊደል አስቆጥሮ
ሳላበቃ ግና
ሳልወርድ ከመቃብር
ቅናት ገነነ
እንደቡና ላርር
ለምን ጣጣ በዛው
ጣፋጭ ንፁህ ፍቅር
ቢታደሉትማ -
ነበር መታደል
እንደሳቁ መኖር ::

No comments: