የአምስተኛ ክፍል የአማርኛ የመማሪያ መጽሐፍ ውስጥ ይመስለኛል ድንቅ የሆነው የ ዘራይ ደረስና የኮለኔል አብዲሳ አጋ በጠላት ሃገር ያሳዩት ጀግንነት ታሪክ በአጭሩ የተዘከረበት:: ብዙዎቻችን ቁንጽል ዕውቀት ስለነዚህ ጀግኖች ቢኖረን እንጂ የጀግንነት ውሎአቸውን በትንታኔ የሚያቀርብ ጽሁፍ አንብበናል ማለት ያስቸግራል:: ይህን ከዚህ በታች ትርጉም የማቀርብላችሁ በጥሩ ሁኔታ ተቀናብሮ የቀረበው የኢትዮጵያዊው ጀግና አብዲሳ አጋ ታሪክ, ቅድሚያ በ እንግሊዝኛ ቋንቋ በዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የተጻፈውን ነው::
ኮሎነል አብዲሳ አጋ የተወለደው በወለጋ ክፍለ ሃገር ነበር:: ወላጅ አባቱ ድንገት ቱግ ብለው ወንድማችውን ገድለው ለፍርድ ሲቀርቡ, የ አስራሁለት አመት ዕድሜ በወቅቱ የነበረው አብዲሳ አባቱን ለማስፈታት አዲስ አበባ በመሄድ ጥረት ቢያደርግም, ከተበየነው ከሞት ቅጣት ሊያድናቸው አልቻለም::በጣም ያዘነውና እንግሽግሽ ያለው ወጣት የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ውስጥ የተቀጠረው ገና የ አስራ አራት አመት ዕድሜው ላይ ነበር:: በ 1936 ከፋሽሽት ጣሊያን ጦር ጋር ፍልሚያ ላይ ተማርኮ ለእስር ጣሊያን ሃገር ሲሲሊ ደሴት ላይ በሚገኘው የማጎሪያ ካምፕ ይታሰራል:: እዚያ ካምፕ ውስጥ ነበር ከዩጎዝላቩ ጀግና ከ ካፒቴን ጁሊዮ ጋር የተገናኘው::
ሁለቱ ጓደኞች ሆነው ከእስረኞች ማጎሪያ ደርዘን የሚሆኑ በማስከተል በድንቅ ሁኔታ አምልጠው ጫካ ተመሸጉ:: ክጥቂት ቀናት በኋላ በጣሊይኖች እጅግ በሚፈራው አብዲሳ እየተመሩ ወደ እስረኛ ማጎሪያው ይመለሰላሉ:: አብዲሳ የካምፑን ጠባቂዎች አንቆ በመግደል, እሱና ጁሊዮ የሞቱትን ወትደሮች ልብስ በመልበስና መሳሪዎቻቸውን በማንገት የፋሺስት ጠባቂ በመምሰል ቀድሞ እስር የነበሩበትን ካምፕ ይቆማሉ:: ከሌሎች የህቡዕ ውጊይ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመሆን ካምፕ ውስጥ ጠልቀው ገብተው እስረኞችን በጠቅላላ ይፈታሉ:: ከፋሺስት መኮንኖች ጋር ተዋግተው ትጥቅና ስንቅ እንዲሁም አንድ የጭነት መኪና ሙሉ የጦር መሳሪያዎችን በመዝረፍ ወደ ጫካ ይመለሳሉ..............ይቀጥላል
No comments:
Post a Comment