Wednesday, November 08, 2006

ምጥን ቀጭን ሽሮ

ምጥን ቀጭን ሽሮ
ኧረ ጉድ ዘንድሮ
ተወዶ ተፈቅሮ
ሰው አይፀድቅ ቆንጥሮ ::

ከሜኑው በፎቶ
ድርት ብሎ ኮርቶ
ታየ ኩሩው ሽሮ
ዶኬ ጥንብርብሮ
ክብሩን አስከብሮ ::

ገላመጥነው ድሮ
አመድ ነዥን ሽሮ
አሁን ተቀይሮ
በእጅግ ተሞሽሮ
እንጀራው ላይ ሰፍሮ
በአይንም ተበላ .......
ላፍ ደባሪው ሽሮ ::

''ሽሮን ሲያታልሏት
ፕሮቲን ነሽ አልዋት ''
ስንል ያፌዝንበት
ይኸው ቀን ወቶሎት
ተናፈቀ በዉነት
እርጉዝ እስኪያስገድድ
ዕምሮት እስኪያስወርድ
ተወዶ እንደጉድ !!

አበው እንዳሉት
ሽሮንም ስናየው፣
ቅል ድንጋይ ይሠብራል
ለሁሉም ጊዜ አለው ::

No comments: