Tuesday, November 07, 2006

ማር ቀረ

ማር ቀረ

በዉነት ማር ቀረ
ስኳር ሽቅብ ናረ ::

በረሀብ እንዳይረግፍ፣
ፅዳቱ እንዳይጎድፍ፣
ዘብ ብትቆም ደጃፍ፣
ዕጥር አርጋው በክንፍ፣
ከቶ አንዳች እንዳያልፍ፣
ከሠራተኛው ረድፍ፣
ገፍቶ ለመጣው ነው ........
ንቢት ብትናደፍ ::

ስለንቦች .......

አኃዝ የለሹ ንብ
ሲርመሰመስ ያለው፣
ሎሌ ለንግስቱ
ለኑሮ መከታው ::
ጥንቁቅ ናት እሷም
እንዲሠምር ሰልፉ ፣
ጥጋብ እንዲበዛ
ማር ሞልቶ እስካፉ፣
ሟች ናት ለቀፎዋ
አይደለችም ክፉ ::

ስለንቦች ......

አይታወቅ በይፋ ፣
ንብ በንብ ሲከፋ፣
አዬ !
ስንቱ አቀረቀረ ፣
የዝንብ ኑሮን ኖረ ፣
በንብ ነኝ ተብዬው ......
ንቡ ተባረረ፣
ቀፎም ጦም አደረ፣
በዉነት ማር ቀረ ! ፣
ስኳር ሽቅብ ናረ ::

No comments: