Monday, November 13, 2006

ጌታ

ፈጣሪ ቢቆጣ
አሣር በዛ ጣጣ
እኛ ባመጣነው
ሰውን አምልከነው
ጌታዬ ብንለው
ይኸው ይኸው
ባሀገር ሟቹ ህዝብ ላይ .....
ባንዳን አንሰራራው ::

ምድር ዛፍ _ ቅጠሉ
እምቢ አለ ሁሉ
ከበረትም ከብቱ
ካውድማ ላይ ምርቱ
የለም ረድኤቱ
ጥሮና ግሮ ሰው
አንዲት ቁና ጠፋ ..........
ጎተራም ዕራበው ::

''ንጉሱ ''ም ሰው ናቀ
ባምላክ ተሳለቀ
ሳቀ ሳቀ ሳቀ
ግና ........
ሰው ተንሰቀሰቀ ::

መዋደድ ጠፋ
ልጅ አባቱን ገፋ
አባት ልጁን ተፋ
ምን ይኖረን ተስፋ
ይኽ አምላክ የለሹ .........
ጨርሶ እስኪጠፋ ::

ባምላክ ታምኖ ወጥቶ
ጠላትን ድል ነስቶ
አንገቱን ያልደፋ
በፋሺሽት ለከፋ
ምነው ዛሬ ምነው .......
ባንዳን አጥፊ ጠፋ ?

ባይኖር ከገበታ
በዕጦት ቢንገላታ
በፋሺሽቶች ፈንታ
ጌታዬ አለው በርታ !
ሀገር አ ድ ሚ ዉን ሰው .....
ያን ምላሰ መንታ ::

No comments: