Friday, December 22, 2006

yemskinu engurguro የምስኪኑ እንጉርጉሮ

Po' Boy Blues
(by Langston Hughes)
funny boxes? click here

ሃገሬ እያለሁ
ወርቃማ ናት ጸሃይ
ሃገሬ እያለሁ
ወርቃማ ናት ጸሃይ
ሰሜን ግን ከመጣሁ
መከራና ስቃይ

ጥሩ ሰው ነበርኩኝ
ክፋት የማልሰራ
አዎን ጥሩ ሰው ነበርኩኝ
ክፋት የማልሰራ
አለም ግን ታከተኝ
መንገዱ ውስብስብ
ክፉ ዘወርዋራ

ደግ ለመሰለችኝ
ወድቄ በፍቅር
ደግ ለመሰለችኝ
ወድቄ በፍቅር
ገንዘቤን አስጨርሳኝ
ለጥቂት
ጨርቄን ጥዬ ነበር

ታከተኝ በጠዋቱ
ታከትኩ ታከትኩ
ታከተኝ ገና በጠዋቱ
ታከትኩ ታከትኩምነው በቀረና
እኔስ ባልተወለድኩ::

(ትርጉም ባቲ)

No comments: