Tuesday, December 19, 2006

tilant ትላንት

funny boxes? click here
እንዳልነበር ጠፋ
የትላንቱ ብሶት
እንዳልታየ ሆነም
መከራና ጭንቀት

ኧረ እንዴት ይርሳል
ሰው ረሳ ግን ቶሎ
በዛሬው በረከት
በሙላት ተታሎ

መቃኘት ብልሃት
አንገትን አዟዙሮ
ዛሬ እንዲቀጥል
እንዳጌጠ አምሮ
ትላንትን እንዳይሆን
ነገ ም ተቀይሮ

ያደፈን ልብ በእንዶድ
ትዕቢቱን አፅድቶ
ለፈጣሪም ለሰው
እጅግ ተመችቶ
አካፍሎም ለሌለው
ከተረፈው ሞልቶ
ማመስገን ጥበብ ነው
ለሚነሳው ሰጥቶ ::

No comments: