Friday, December 15, 2006

libe yabeba massaልቤ የአበባ ማሳ

funny boxes? click here

ፈገግታሽ ፀሀይን
ቃሎችሽም ዝናብ

ልቤ የአበባ ማሳ
ቢያምር ባንቺ ቢዋብ ::

አያሌ አበቦች
ከልቤ ውስጥ ፈልተው

ዕፁብ ድንቅ ሆድዬ
አቤት ማማራቸው ::

ነጭ ቀዩ .... ሞልቶ
ሁሉም በአይነት አይነቱ

የፅጌረዳን ድምቀት
መጥተሽ ቃኚው እቱ ::

ላስጎብኝሽ ላሳይሽ
ፍቀጅልኝ በቃ

ማኖሪያ ነው ልብሽ
ድንቅ የአበቦች ዕቃ !

No comments: