Tuesday, December 05, 2006

Awasa አዋሳ

funny boxes? click here

ተዛምዳ ከጀንበር
ጉድ 'ኮ ሰራችኝ ,
አዋሳ ሐይቅ ዳር
አፍዝዛ አስቀረችኝ ;

ፔዳሉን ታፍጥነው
ትምጥልኝ ንገሯት ,
አውቃለሁ እንደናትዋ
ሳይክል ጋላቢ ናት

ትመስላለች ልጅት
የምሽቷን ጀንበር ,
ፈንጥቃ ከሰማይ
ሰምጣ ከውሀ ምትቀር ;
እድገቷ አዋሳ
ጠላቂ ዋናተኛ ,
ከውሀ ሳትንሳፈፍ
ከቶ ማትተኛ ,
አጣሁላት እኔስ
ማድነቂያ አማርኛ

ድረሺለት በሏት
በሞሸራት እግዜር ,
ከሐይቁ ሳታርፍ
ጠላቂቱ ጀንበር

ብስክሌትዋ ይፍጠን
ንገሯት ንገሯት ,
መንፈስ የሚገዛ
የዋህነት አላት ;
ተዛምዳ ከጀንበር
ጉድ አደርገችኝ ,
አዋሳ ሀይቅ ዳር
በፍቅር አሰረችኝ ::

No comments: