Friday, December 01, 2006

ነገስታት (እቴጌ ) ዘ ኢትዮጵያ

(EMPRESSE OF ETHIOPIA)
CANDACE
........ካለፈው የቀጠለ

ግብጽ የነገሰው የመጨረሻው ኩሽ(ኢትዮጵያ )ፈርኦን በጦርነት ድል በተደረገ ጊዜ, ያኔ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ በነበረችው ናፓታ (ማራው) ነበር ፍርኦን ታውታሞን የሸሸው:: ይህች ከተማ የሮማውያን ሃይል እስከየት መሆኑን ለክታ ማሳየት የተቻልትን ሃያል ካንድክ (CANDACE) አስነስታለች:: ታሪክ ጸህፊዎች ጡንቸኛ በማለት ጥንካሬዋን የሚነግሩላት ንግስተ ኢትዮጵያ , ጦር ሜዳ ፍልሚያ ላይ አንድ አይኗ የተጎዳ አይናማ ነበረች::
የነጭ እና ጥቁር አባይ መነሻ ማወቅ የወደዱት ሮማዊውያን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ማለፍ ነበረባቸው, ልክ ግብጽን በጣር ሃይላቸው እንዳስገበሩ ኢትዮጵያንም አስገብረው:: ንግስቲቱ አጼ ኦውገስተስ የላካቸውን ወታደሮች አባይ ትወጣን አስዋን ላይ የሮማውን ጦር ፍልሚያ ገጥማ ድል ታደርጋለች; የኦገስተስ ምስልን የያዘ ሃውልት በሙሉ በወታደሮችዋ እንዲወድም ይሆናል::

ሮማውያኖች ሃይላቸውን እንደገና አጠናክረው የመልሶ ማጥቃት ለማድረግ እስከ ናፓ ኢትዮጵያ ቢገቡም ዕቅዳቸው አልሰራ ለሁለተኛ ጊዜ:: ይህኛው ከቀድሞ የሮማን ጦር ይልቅ ከፍተኛ ውርደትን ተከናንብቦ ነበር:: ኢትዮጵያን በወረራ ድል የማድረጉን ጉዳይ ወደኋላ ተደርጎ ማስተባበያ እንዲሆን የኢትዮጵያዋ ንግስት ሰላም በመጠየቅዋ ንጉሰነገስት ኦውገስተስ ፈቅደዋል ሲባል ተነገር::

For More Details On The Article

No comments: