Thursday, November 23, 2006

saw a`yer ሰው አየር

funny boxes? click here

የአይኖቹ ሲሳይ ፣
አንጋጦ ሰማይ ሲያይ፣
ለምድር በ ምድር ፣
ሲጥር ና ሲግር ፣
አቅሉ ጥምጣም ሲዞር ::

ለጥላቻ ቆርጦ፣
ለበቀልም ሮጦ ፣
አቤት ጥድፊያው ለክብር፣
ደሙም ሲፈስ ለፍቅር ፣
ላመነበት ሲኖር ፣
የሰው ልጅ በምድር ::

እንደምድር ለካስ፣
ያሸበረቀው ዳስ ፣
የማያውቀው ስፍራ፣
ስሙ የሚያሰፈራ ፣
ቤቱ ለካስ ነበር ፣
እንደ ውዱ ምድር ፣
የሰማዩም ሃገር ::

በሀሳብ መንኩራኩር ፣
ጭልጥ ብሎ ሲበር ፣
በህልሙ ተውልዶ ፣
ርቆ ከምድር ሄዶ ፣
አወቀ -
የአዳም ዘር ፣
ገላ ልብሱ አፈር ፣
መርገፉ እንደማይቀር ::

ስጋ የለሽ መንፈስ ፣
እንደንፋስ የሚነፍስ፣
እንደሚሆን አየር ፣
አፈር ልብሱ ሲቀር፣
ስው አየር
ሰው አየር ::

No comments: