Friday, November 17, 2006

ወደድኩሽ ውደጂኝ

ብዕር ከወረቀት
ማሳሳም ተስኖኝ
የመውደድ ደብዳቤ
አልወለድ ብሎኝ
ቀለም ወረቀት ላይ
ገና አላሸበረቀ
ቃላት በ ቃላት ላይ
ቃልን እያረቀ ::

አንዱ ቃል ከ ሌላው
ልቤ ውስጥ ሲራኮት
ደብዳቤ ለመፃፍ
ለአካል ሙናዬ ውቢት
ሞቀልኝ ገበያው
የፍቅር ቃላቱ
ሲተራመስ አየሁ
ቅኔ ም በአይነት አይነቱ
የቃላት ዕሩምታው
አላከትም ቢለኝ
'እኔን ምረጥ እኔን '
የሚሉም መሰልኝ ::

ሁሉም ቆንጆ መላክ
ብቃት የታደሉ
'እኔ ልሸከም ፍቅር
እኔን ምረጥ ' ያሉ
ጉጉታቸው ልቆ
"እኔ ልቅደም ' 'የለም እኔ ' ቢሉ
ከ ወደድኩሽ _ውደጂኝ
ጭራሽ ! አይስተካከሉ ::

No comments: