Wednesday, November 29, 2006

ነገስታት (እቴጌ ) ዘ ኢትዮጵያ

(EMPRESSES OF ETHIOPIA)

ኢትዮጵያ በጥንታዊነትዋን ቀደምት መሆንዋን የሚመሰክሩላት አበይት የታሪክ ምስክሮች አሉ :: የነበሩዋት ሥርወ -መንግስትታት ወይም ዳይናስቲስ በህግና በመንግስት አወቃቀር ና ስርዐት ህዝቦችዋ ከጥንት ጀምሮ የበላይነትን ስፍራ መያዛቸውን ይናገራሉ :: ሦስት ሺህ ዘመን ብለን የምንቆጥረው እንግዴ ከ ንግስተ ሳባ , መክዳ , ና ከንጉስ ሰለሞን ልጅ ንጉስ ቀዳማዊ ሚኒሊክ (=የንጉስ ልጅ ) ጀምረን እስከ ቀዳማዊ ኃ /ሥላሴ የነበረውን ዘመን ብቻ ነው :: ከሦስት ሺው ዘመናት በፊት የነበረችው ኢትዮጵያ እንደምን ነበረች የሚለውን አትኩሮት ጉልህ አድርጎ ማሳየት ነው የዚህ መጣጥፍ ግንባር ቀደም ሚና :: ( ታሪክን ወደኋላ ሄደን ስንመረምር የቀድሞዋ ኢትዮጵያ የመንን , ሊቢያን , የታችኛው አባይ /ናይል ና ከፊል /በጠቅላላ ሱዳንን ጭምር የምታጠቃልል መሆንዋን ከግንዛቤ ማስገባት ሊኖርብን ነው )::

የካንዳንስ (= የንግስቶች የንግስና የማዕረግ መጠሪያ ስም ) ዘመኖችን ኢትዮጵያ አሳልፋለች :: ወንዶች ነገስታት በሦስት ሺህ ው ዘመነናት ውስጥ እንደተፈራረቁ ሁሉ ከዚያ በፊት ንግስቶች በማያቋርጥ ሁኔታ ዘጠና ሰባት የሚደርሱ የተከበሩና የተፈሩ ሀያላን ከንግስት መክዳ ቀደም ብለው ገዝተዋል ::
በዝነኛነታቸው በጦርነት ስልት አዋቂነታቸው ታሪክ ሁሌ የሚያነሳቸው የነበሩም ነበሩ :: የነዚህ ንግስቶች ንግስና ያበቃው ይላሉ ጸሃፊዎች መክዳ , ንግስተ ሳባ ላይ እንደሆነ ይናገራሉ :: ኃያላን ስለምሆናቸው የተመዘገበ ለምሳሌ ያንዲቱን ታሪክ ይህን ይመስላል :: አለክሳንደር አለምን በማን አለብኝነት ሲያንበርክክ ና ክብርና ዝናን ሲቀዳጅ , በወቅቱ የኢትዮጵያ ካንደንስ (ንግስት ) የነበረችው በአለም ላይ በጦርነት ውጊያ መላቸው የአንቱታን ማዕረግ ከተቀዳጁት ጥቂት ተዋጊዎች አንዷ ነበረች :: ግብጽን (የላይኛው ?) አስገብሮ በጉጉት ይጠብቀው የነበረውን ና በንግስቲቱ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በተጠንቀቅ የሚጠብቀውን የጥቁር ጦር ግን ኢትዮጵያን በመውረር መገናኛት አለክሳንደር ምርጫው አላደረገውም :: ያለውን ክብርና ሞግስ የማጣቱ በተለይ ደግም በሴት ጄነራል ከስጋት ጥሎት ነበር ::

ኢትዮጵያ በንግስቶች ዘመን በሃብት ና በኃይል የጠነከረች መሆንዋ ብቻ ሳይሆን እስከአሁን ድረስ ስማቸው የሚነገርላቸው የአውሮፓ የቅኔ ሰዎች በቅኔዎቻቸው አሞግሰዋታል :: በቅዱሳን መጻህፍት ስለፍርድ አዋቂዎቹ ስለሰለጠኑት ስለድንቆቹ ኢትዮጵያዊያን በተለያዪ ስፍራዎች በተለይ በመጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን ውስጥ አይሌ ስፍራ ሰፍረው ይገኛሉ :: በሃዲስ ኪዳንም የአንዲቱን ካንደስ ንግስተ ኢትዮጵያ ታሪክ የሚዘክር በ ሃዋርያት ሥራ 8:27 ተጠቅሶ ይገኛል ::
ይቀጥላል .........amargna

No comments: