Wednesday, October 04, 2006

kibur medrek Ethiopian :: View topic - Bati's Poems

Could't Veiw Amargna? Download Free Geez Unicode Software
እኔ ምን አውቃለሁ

አንቺን እና እኔን
ለሁለት ሲከፍለን
አንድ ሙሉ አፕል -
መሰለኝ የነበርን
እኔን አንቺን አርጎ -
አቺንም እኔን
አንቺ እኔን እኔን
እኔም አንቺን አንቺን ::
ለምን ?
እኔ ምን አውቅለሁ ::

እሳት ልቤ ጭሮ
ማጥፊያን ካንቺ ቀብሮ
የፍቅር ፈጣሪ
በፍቅር ተፈሪ
በፍቅር ተከባሪ
ሲጠራም ተፈቅሮ
ፍቅር በኛ አኑሮ

ልቤ ካንቺ ደርት
ሂዶ ቢሰንብት
አንጎሌን ካንቺ ጋ
ሲባክን ፍለጋ
አንጎሌ ሊያወራው
ልቤ ን -
ከጡትሽ ስር ካለው
ያንቺ ም ከኔ ደረት
መኖሪያው ሞቆለት
ቃላችን አንድ አይነት
ስሜታችን-
ቢውሉ ለዕይታ
ተመሳሳይ መንታ
ለምን ?
እኔ ምን አውቃለሁ
ጠይቂ ፈጣሪን
እኔም ጠይቃለሁ ::

No comments: