Monday, October 30, 2006

አበባ _ከ _ማሩ

አበባ _ከ _ማሩ

መላዕክት ስም አወጡ
ያይኔ አበባ አልዋት
በዕውነት ከአበባ
በላጭ መስህብ አላት ::

ልዩ ሰው ለኔማ
ደማቅ ፍቅር አበባ
ፅጌረዳን ውበት
ብቅ ያለች ደራርባ ::

እማኝ ህዋሶቼ
ሲታጠንዋት ዋሉ
በመአዛዋ ርቀው
ጠፍቶባቸው ውሉ ::

ለደማቅዋ አበባ
ንብ ሁን አለኝ ልቤ
ቅስም ቅምስ ላደርግ
አይቀርቡን ቀርቤ ::

ልቤ ግን ቸኮለ
ሊሆን የማር ቀፎ
በእንኳን ደህና መጣሽ
ሊያሳድራት አቅፎ
አባባ _ከ _ማሩ
ቢታየው ተንሳፎ ::

No comments: