Friday, October 13, 2006

ማን ይሉት ቋንቋው

Posted: Tue Jan 31, 2006 11:58 pm Post subject: ማን ይሉት ቋንቋው

ማን ይሉት ቋንቋው

ማን ይሉት ቋንቋው
ውበትሽን መግለጫ ,
ከዕንቁ የላቀ ዕንቁን
ትንታኔ መስጫ

ዝምታ ነው መልሴ
ስላንቺ ብጠየቅ ,
ምንም ቃል የለኝ
ፀጋሽን ለማድነቅ

ገነት ገነትዬ
ልበል በጥቅሉ ,
ቋንቋ አልተፈጠረም
የሚገልፅሽ ቃሉ

እንጎቻሽ ሸጋ
ፍሬሽም ጣፋጭ ,
ትትና ደግነት
ከልብ የሚያመነጭ

ማን ይሉት ቋንቋው
አንቺን የመግለጫ ,
ከፍቅር የላቀ ፍቅርን
ትንታኔ መስጫ

ገኒዬ ገኒዬ
አለሁልህ በይኝ ,
በፈጠርሽ አምላክ
ቋንቋሽን አውሽኝ ,
ከ 'አፈቀርኩ ' ሽ ዕሚልቅ
ተንፍሼ ይውጣልኝ ::

No comments: