Tuesday, September 26, 2006

WARKA :: View topic - ...ከገጠመ ግጥም------>[ካይኔ ተደብቃ]#180016#180016

ካይኔ ተደብቃ

አለው ነገር አይኗ
ድምፅዋም ነገር አለው፣
ደነገጥኩ ከልቤ
ይህ ለኔ አዲስ ነው ::

ጠለቀች ይኽች ፀሀይ
ካይኔ ተደብቃ ፣
የአቅሌን ሰውነት
ልቤን አስጨንቃ ::

በራች ቦግ ብላ
ጨረርዋን ፈንጥቃ፣
ካልደመቀች እሷ
እንደማልኖር አውቃ ::

በተራዬ እንደምድር
ለእሷ ብንቀሳቀስ፣
የሽምጥ ጋለበ
ፍቅር እንደፈረስ፣
ይዞ ጭልጥ ባዩ
እያረገ ፍልሥሥ::

No comments: