Friday, September 15, 2006

kibur medrek Ethiopian :: View topic - Bati's Poems

ፊት ና ፍትፍትሽፍትፍቱና ፊትሽ
ባንድነት ቢመጡ
ድንብርብሬ ወጥቶ
ጠፋኝ መላ ቅጡ::
የነፍሴ ምግብ ነው
ግሩም ጨዋታሺ
ነጻ ማ ስትሆኚ
አቤት ስትፈውሺ::

የአካሌ ምርኩዝ ነው
ፍትፍቱ የጣትሽ
ጉልበቱ የልቤ
የሙጢኝ ያለሽ::

ፊት ና ፍትፍትሽ
ሆኖ አነባበሮ
ልቤ ርቆኝ ጠፋ
ካንጀቴ ተቀብሮ::
ፈትሽው ልብሽን
በናትሽ አንቺዬ
ኑሮዬ አይደል ከዚያ
ፍልሥሥ ብዬ::

ነጭ ጽጌረዳ
ቀዮች የደመቁ
በቅለዋል ከውስጤ
በፍቅር ረቂቁ::
እስቲ ልላክልሽ
አንዲቱን መዝዤ
አልቻልኩም ብቻዬን
በፍቅርሽ ደንዝዤ::

No comments: